Тексты
ከአባይ መፍለቂያ ከብዝሃን ግርግም
ነበረ.......
ሀበሻ የሚባል አሳ መሳይ ጠይም(2x)
ውብ የሆነው መልኩ
ነበር ተሸክሞ ፍቅርን በልኩ
ኪዳኑን አድርሶ
የጌታውን ታቦት በልቡ አንግሶ
ትሁት ሆኖ ሳለ
በጥቁር ሰሌዳ ፍቅርን እየሳለ
ይኖር የነበረ
ሳለ ብዙ ሆኖ በአንድ ክንድ ያበረ
ሀበሻ የሚባል ስሙ የሚያስፈራ
ጠይም አሳ መሳይ ጅንን ያለ ኮራ
......
ከአባይ መፍለቂያ ከብዝሃን ግርግም
ነበረ.......
ሀበሻ የሚባል አሳ መሳይ ጠይም(2x)
እንዲህ እንደዛሬ ክንዱ ሳይዝል በፊት
ስጋ ለለበሰ ነበር ትልቅ ምኞት
ነበረ ነበረ ነበረ
በፊት ነበረ
ከአባይ መፍለቂያ ከብዝሃን ግርግም
ነበረ....
ሀበሻ የሚባል አሳ መሳይ ጠይም(2x)
ሳይጮህ የአቤል ደም
ቃየልም ሳይገኝ ከጥላቻ ግርግም
ሳይሞት የፍቅር ዘር
ጠይም አሳ መሳይ አንድ ሀበሻ ነበር ።
ነበረ.......
ሀበሻ የሚባል አሳ መሳይ ጠይም(2x)
ውብ የሆነው መልኩ
ነበር ተሸክሞ ፍቅርን በልኩ
ኪዳኑን አድርሶ
የጌታውን ታቦት በልቡ አንግሶ
ትሁት ሆኖ ሳለ
በጥቁር ሰሌዳ ፍቅርን እየሳለ
ይኖር የነበረ
ሳለ ብዙ ሆኖ በአንድ ክንድ ያበረ
ሀበሻ የሚባል ስሙ የሚያስፈራ
ጠይም አሳ መሳይ ጅንን ያለ ኮራ
......
ከአባይ መፍለቂያ ከብዝሃን ግርግም
ነበረ.......
ሀበሻ የሚባል አሳ መሳይ ጠይም(2x)
እንዲህ እንደዛሬ ክንዱ ሳይዝል በፊት
ስጋ ለለበሰ ነበር ትልቅ ምኞት
ነበረ ነበረ ነበረ
በፊት ነበረ
ከአባይ መፍለቂያ ከብዝሃን ግርግም
ነበረ....
ሀበሻ የሚባል አሳ መሳይ ጠይም(2x)
ሳይጮህ የአቤል ደም
ቃየልም ሳይገኝ ከጥላቻ ግርግም
ሳይሞት የፍቅር ዘር
ጠይም አሳ መሳይ አንድ ሀበሻ ነበር ።